This platform is under active development. Powered by Ollama (Qwen2.5 3B Instruct) with bge-m3 embeddings.Learn more

የቤት ኪራይ ውል (Amharic)

ቀን፡ //20 ዓ.ም.

የመኖሪያ ቤት ኪራይ ሞዴል ውል

1. አከራይ
ስም ከነአያት፡
የመኖሪያ አድራሻ፡- ክልል ከተማ ፤ ክፍል ከተማ
ወረዳ/ቀበሌ ልዩ ቦታ፡ ፣ የቤት ቁጥር፡ ስልክ ቁጥር፡
2. ተከራይ ስም ከነአያት፡ የመኖሪያ አድራሻ፡- ክልል ከተማ ፤ ክፍለ ከተማ ወረዳ/ቀበሌ፡ ሌዩ ቦታ፡ ፣ የቤት ቁጥር ስልክ ቁጥር፡
3. የሚከራየው መኖሪያ ቤት አድራሻ፡ ክልል፡ ከተማ፡ ፤ ክፍለ ከተማ፡ ወረዳ/ቀበሌ
ልዩ ቦታ፡ የቤት ቁጥር፡ ባለቤትነቱ የ የሆነና ለመኖሪያ ቤት አገልግልት የሚውል (ራሱን የቻለ ግቢ፣ ክፍል ቤት)
4. የኪራይ ሁኔታ፡
1) የኪራይ ቤቱ ሁኔታ፡ (ነባር የኪራይ መኖሪያ ቤት፣ አዲስ የተገነባ የኪራይ መኖሪያ ቤት፣ ነባር ተከራይቶ የማያውቅ የኪራይ መኖሪያ ቤት)
2) አከራይ ከላይ የተጠቀሰውን መኖሪያ ቤት በብር ( ብር) ለ ዓመት (የመኖሪያ ቤት ኪራይ የውሉ ዘመን ከሁለት ዓመት ሊያንስ አይችልም) ለተከራይ ለማከራየት ተከራይም መኖሪያ ቤቱን በዚሁ ዋጋ ለመከራየት በመስማማት ይህንን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዉል ስምምነት ተዋውለናል።
3) ይህ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የኪራይ ውሉ ዘመኑ ሲያበቃ በአከራይና ተከራይ ስምምነት በጽሑፍ ሊታደስ ይችላል።
4) የውሃ፣ የስልክ፣ የመብራት፣ የጥበቃ፣ የፅዳት ወይም ሌሎች መሰል አገልግልቶች ክፍያ የሚከፍለው ይሆናል። (ተከራይ ወይም አከራይ ወይም አብረው)
5. የአከራይ ግዴታዎች
1) አከራይ በውል ስምምነቱ ላይ ከተመለከተው የመኖሪያ ቤቱ ኪራይ ዋጋ ጭማሪ ማድረግ የሚችለው በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መሠረት ተቆጣጣሪው አካሉ በየዓመቱ የሚያደርገውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ መሰረት በማድረግ ብቻ ይሆናል።
2) አከራይ በተቆጣጣሪው አካሉ የተደረገውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ መሰረት በማድረግ የውል ዘመኑ ባላለቀ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ላይ ጭማሪ ያደረገ እንደሆነ የተደረገውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ ለተከራይ እና ለተቆጣጣሪው አካል በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት።
6. የተከራይ ግዴታዎች
1) የመኖሪያ ቤቱን ሲከራይ ቅድሚያ ክፍያ ወር (የአንድ ወር /የሁለት ወር) የመኖሪያ ቤት ኪራይ ብር ( ) በዛሬዉ ዕለት ለአከራይ ከፍያለሁ። ከዚህ በኋላ ያለዉ አከፋፈል ቅድሚያ የሚከፈል ሆኖ ወርሃዊ ክፍያ በየወሩ ወር በገባ እስከ ቀን ለመክፈል ተስማምቻለሁ።
2) ተከራይ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መሰረት ተቆጣጣሪው አካሉ የወሰነውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ ማሻሻያ መነሻ በማድረግ አከራይ የሚጨመረውን የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ በዚህ ውል ላይ የተመለከተው የኪራይ ዋጋ ላይ በመጨመር ይከፍላል።
3) ተከራይ የዚህ የኪራይ ውል ዘመን ሳይጠናቀቅ የመኖሪያ ቤቱን መልቀቅ ቢፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ ለአከራዩ የመስጠት ግዴታ አለበት።
4) ተከራይ የመኖሪያ ቤቱን በአግባቡ ጠብቆና ጉዳት ሳያደርስ የመኖሪያ ኪራይ ውሉ ሲያበቃ በተረከበበት ሁኔታ ለአከራይ የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።
5) ተከራይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ክፍያ በባንክ ወይም በሌላ ህጋዊ በሆነ የኤላክትሮኒክ ዘዴ ብቻ መፈጸም አለበት።
በዚህ ውል ባልተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 ተፈጻሚ ይሆናል።
ይህ ውል በአከራይና በተከራይ ተፈርሞ በተቆጣጣሪው አካሉ ሲረጋገጥ የፀና ይሆናል።
አከራይ ስም፡
ፊርማ፡ ________________________________
ቀን፡
ተከራይ ስም፡
ፊርማ፡ ________________________________
ቀን፡
የእማኞች ስምና ፊርማ
1) ስም ፊርማ ____________________ ቀን
2) ስም ፊርማ ____________________ ቀን
3) ስም ፊርማ ____________________ ቀን